bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 36
Psalms 36
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ክፉውን ሰው፣ በደል በልቡ ታናግረዋለች፤ እግዚአብሔርን መፍራት፣ በፊቱ የለም፤
2
በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና።
3
ከአንደበቱ የሚወጣው የክፋትና የተንኰል ቃል ነው፤ ማስተዋልንና በጎ ማድረግን ትቷል።
4
በመኝታው ላይ ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ራሱን በጎ ባልሆነ መንገድ ይመራል፤ ክፋትንም አያርቅም።
5
እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል፤ ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል።
6
ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች፣ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ።
7
አምላክ ሆይ፤ ምሕረትህ እንዴት ክቡር ነው! የሰዎች ልጆች ሁሉ፣ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ።
8
ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ።
9
የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፣ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
10
ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ ዘወትር አይቋረጥባቸው።
11
የትዕቢተኛ እግር በላዬ አይምጣ፤ የክፉውም ሰው እጅ አያሳድደኝ።
12
ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት!
← Chapter 35
Chapter 37 →