bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 28
Psalms 28
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤ አንተ ዝም ካልኸኝ፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ።
2
ለርዳታ በጮኽሁ ጊዜ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ፣ እጆቼን በዘረጋሁ ጊዜ፣ የልመናዬን ቃል ስማ።
3
በልባቸው ተንኰል እያለ፣ ከባልንጀሮቻቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ፣ ከክፉ አድራጊዎችና ከዐመፃ ሰዎች ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ።
4
እንደ ሥራቸው፣ እንደ ክፉ ተግባራቸው ክፈላቸው፤ እንደ እጃቸው ሥራ ስጣቸው፤ አጸፋውን መልስላቸው።
5
ለእግዚአብሔር ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ ለእጆቹም ተግባራት ስፍራ ስላልሰጡ፣ እርሱ ያፈርሳቸዋል፤ መልሶም አይገነባቸውም።
6
የልመናዬን ቃል ሰምቷልና፣ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን።
7
እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።
8
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።
9
ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።
← Chapter 27
Chapter 29 →