bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 26
Psalms 26
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣ አንተው ፍረድልኝ። ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ።
2
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤ ልቤንና ውስጤን መርምር፤
3
ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣ በእውነትህም ተመላለስሁ።
4
ከማይረቡ ጋር አልተቀመጥሁም፤ ከግብዞችም ጋር አልተባበርሁም።
5
የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤ ከዐመፀኞችም ጋር አልቀመጥም።
6
እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤
7
የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣ ታምራትህንም አወራ ዘንድ ነው።
8
እግዚአብሔር ሆይ፤ የምትኖርበትን ቤት፣ የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9
ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋር፣ ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋር አታስወግዳት።
10
በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ፤ ቀኝ እጃቸውም ጕቦን ያጋብሳል።
11
እኔ ግን በተአማኒ ሕይወት እጓዛለሁ፤ አድነኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ።
12
እግሮቼ በደልዳላ ስፍራ ቆመዋል፤ በታላቅ ጉባኤ መካከልም እግዚአብሔርን እባርከዋለሁ።
← Chapter 25
Chapter 27 →