bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 24
Psalms 24
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤
2
እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤ በውሆችም ላይ አጽንቷታል።
3
ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
4
ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤ ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤ በውሸት የማይምል፤
5
እርሱ በረከትን ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ ምሕረትንም ከአዳኝ አምላኩ ይቀበላል።
6
እርሱን የሚፈልግ ትውልድ እንዲህ ነው፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ፊትህን የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው።
7
እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤ እናንተ የዘላለም በሮች፤ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
8
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኀያል፤ እግዚአብሔር ነው በውጊያ ኀያል።
9
እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤ እናንተ የዘላለም በሮች፤ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
10
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የሰራዊት አምላክ ፣ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።
← Chapter 23
Chapter 25 →