bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 20
Psalms 20
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤ የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።
2
ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤ ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።
3
ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ።
4
የልብህን መሻት ይስጥህ፤ ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።
5
በአንተ ድል ደስ ይበለን፤ በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ።
6
እግዚአብሔር ፣ የቀባውን እንደሚያድን አሁን ዐወቅሁ፤ የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣ ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።
7
እነዚህ በሰረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤ እኛ ግን ትምክሕታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።
8
እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፤ ጸንተንም ቆምን።
9
እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥን አድን፤ እኛም በጠራንህ ቀን ስማን።
← Chapter 19
Chapter 21 →