bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 143
Psalms 143
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ልመናዬን አድምጥ፤ በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ ሰምተህ መልስልኝ።
2
ሰው ሆኖ በፊትህ ጻድቅ የለምና፣ ባሪያህን ወደ ፍርድ አታቅርበው።
3
ጠላት እስከ ሞት አሳድዶኛል፤ ሕይወቴንም አድቅቆ ከዐፈር ቀላቅሏል፤ ቀደም ብለው እንደ ሞቱትም፣ በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል።
4
ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ዝላለች፤ ልቤም በውስጤ ደንግጧል።
5
የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ፤ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ አውጠነጠንሁ።
6
እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
7
እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤ መንፈሴ ደከመች፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።
8
በአንተ ታምኛለሁና፣ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
9
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መሰወሪያ አድርጌአለሁና፣ ከጠላቶቼ አድነኝ።
10
አንተ አምላኬ ነህና፣ ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ፤ መልካሙ መንፈስህም፣ በቀናችው መንገድ ይምራኝ።
11
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራ አውጣት።
12
ጠላቶቼንም ለእኔ ስላለህ ምሕረት ደምስሳቸው፤ እኔ ባሪያህ ነኝና፣ ነፍሴን የሚያስጨንቋትን ሁሉ አጥፋቸው።
← Chapter 142
Chapter 144 →