bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 141
Psalms 141
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ ወደ አንተ ስጣራም ድምፄን ስማ።
2
ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ፤ እጄን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።
3
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
4
ከዐመፀኞች ጋር፣ በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣ ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤ ከድግሳቸውም አልቋደስ።
5
ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፤
6
ሹማምታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፤ ቃሌ የምታረካ ናትና ይሰሟታል።
7
ደግሞም፣ “ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣ እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል አፋፍ ላይ ተበታተነ” ይላሉ።
8
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።
9
ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣ ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ።
10
እኔ ብቻ በደኅና ሳመልጥ፣ ክፉዎቹ በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ።
← Chapter 140
Chapter 142 →