bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 14
Psalms 14
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤ በጎ ነገር የሚሠራ አንድም የለም።
2
የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ መኖሩን ለማየት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3
ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ በአንድ ላይም ብልሹ ሆነዋል፤ አንድ እንኳ፣ መልካም የሚያደርግ የለም።
4
የእግዚአብሔርን ስም የማይጠሩት፣ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ዕውቀት የላቸውምን?
5
ባሉበት ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና።
6
እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።
7
ምነው እስራኤልን የሚያድን ከጽዮን በወጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣ ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።
← Chapter 13
Chapter 15 →