bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 137
Psalms 137
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።
2
እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣ በገናዎቻችንን ሰቀልን።
3
የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤ የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።
4
የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!
5
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ ቀኝ እጄ ትክዳኝ።
6
ሳላስታውስሽ ብቀር፣ ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ ምላሴ ከትናጋዬ ጋር ትጣበቅ።
7
እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።
8
አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤ በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሽው ድርጊት፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ የተመሰገነ ነው፤
9
ሕፃናትሽንም ይዞ፣ በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ የተመሰገነ ነው።
← Chapter 136
Chapter 138 →