bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 135
Psalms 135
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርን ስም ወድሱ፤ እናንት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤
2
በእግዚአብሔር ቤት፣ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት።
3
እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤
4
እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣ እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጧልና።
5
እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፣ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።
6
በሰማይና በምድር፣ በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ሁሉ ያደርጋል።
7
እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤ መብረቅ ከዝናብ ጋር እንዲወርድ ያደርጋል፤ ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል።
8
በኵር ሆኖ በግብፅ የተወለደውን፣ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ቀሠፈ።
9
ግብፅ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣ በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ።
10
ብዙ ሕዝቦችን መታ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
11
የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፣ የባሳንን ንጉሥ ዐግን፣ የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፤
12
ምድራቸውንም ርስት አድርጎ፣ ለሕዝቡ ርስት እንዲሆን ለእስራኤል ሰጠ።
13
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህ ዘላለማዊ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
14
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፣ ለአገልጋዮቹም ይራራላቸዋል።
15
የአሕዛብ ጣዖታት ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣ የሰው እጅ ያበጃቸው ናቸው።
16
አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ ዐይን አላቸው፤ አያዩም፤
17
ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤ በአፋቸውም እስትንፋስ የለም።
18
እነዚህን የሚያበጁ፣ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
19
የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ የአሮን ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤
20
የሌዊ ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።
21
በኢየሩሳሌም የሚኖር እግዚአብሔር ፣ ከጽዮን ይባረክ። ሃሌ ሉያ።
← Chapter 134
Chapter 136 →