bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 124
Psalms 124
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እስራኤል እንዲህ ይበል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣
2
ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣
3
ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣ በቁመናችን በዋጡን ነበር፤
4
ጐርፍ ባጥለቀለቀን፣ ፈረሰኛው ውሃ ባሰጠመን፣
5
ደራሽ ውሃም ጠራርጎ በወሰደን ነበር።
6
በጥርሳቸው ከመዘንጠል የጠበቀን፣ እግዚአብሔር ይባረክ።
7
ነፍሳችን እንደ ወፍ፣ ከዐዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም አመለጥን።
8
የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ የእግዚአብሔር ስም ረዳታችን ነው።
← Chapter 123
Chapter 125 →