bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 12
Psalms 12
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ደግ ሰው የለምና አንተው ድረስልኝ! ከሰዎችም መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም።
2
እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ።
3
ሸንጋዩን ከንፈር ሁሉ፣ ነገር የምታበዛውንም ምላስ እግዚአብሔር ያጥፋ!
4
እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?” የሚሉ ናቸው።
5
እግዚአብሔር ፣ “ስለ ድኾች መከራ፣ ስለ ችግረኞችም ጩኸት፣ አሁን እነሣለሁ፤ በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።
6
የእግዚአብሔር ቃል የጠራ ቃል ነው፤ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ፣ በምድር ላይ በከውር እንደ ተፈተነ ብር ነው።
7
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤ ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ።
8
በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣ ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።
← Chapter 11
Chapter 13 →