bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 116
Psalms 116
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት።
2
ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
3
የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤ የሲኦልም ጣር አገኘኝ፤ ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።
4
እኔም የእግዚአብሔርን ስም ጠራሁ፤ “ እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።
5
እግዚአብሔር ቸርና ጻድቅ ነው፤ አምላካችን መሓሪ ነው።
6
እግዚአብሔር ገሮችን ይጠብቃል፤ እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።
7
ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና፤
8
አንተ ነፍሴን ከሞት፣ ዐይኔን ከእንባ፣ እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።
9
እኔም በሕያዋን ምድር፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ።
10
“እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣ እምነቴን ጠብቄአለሁ።
11
ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
12
ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ምን ልክፈለው?
13
የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
14
በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።
15
የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።
16
እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤ እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፤ ከእስራቴም ፈታኸኝ።
17
ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
18
በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ፤
19
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ። ሃሌ ሉያ።
← Chapter 115
Chapter 117 →