bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 108
Psalms 108
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አምላክ ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ እዘምራለሁ፤ በፍጹም ነፍሴም እዘምራለሁ።
2
በገናም መሰንቆም ተነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
3
እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሕዝቦችም መካከል እዘምርልሃለሁ።
4
ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤ ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ትደርሳለች።
5
አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።
6
ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣ በቀኝ እጅህ ታደግ፤ መልስልኝም።
7
እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ አለ፤ ደስ እያለኝ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤ “የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።
8
ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ።
9
ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤ በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እፎክራለሁ።”
10
ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምያስስ ማን ያደርሰኛል?
11
እግዚአብሔር ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋር አልወጣ አልህ!
12
አሁንም የሰው ማዳን ከንቱ ነውና፣ በጠላታችን ላይ ድልን አቀዳጀን።
13
እግዚአብሔር ሲረዳን ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንንም ከእግሩ በታች የሚረግጥ እርሱ ነው።
← Chapter 107
Chapter 109 →