bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Psalms 102
Psalms 102
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።
2
በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ።
3
ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤ ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።
4
ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤ እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።
5
ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣ ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋር ተጣበቀ።
6
የምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤ በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጕጕት ሆንሁ።
7
ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ በቤቴ ጕልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።
8
ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤ የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።
9
ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤ መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁ።
10
ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።
11
ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
12
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
13
ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፣ ለእርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤ የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል።
14
አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ ለዐፈሯም ይሳሳሉ።
15
ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣ የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።
16
እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤ በክብሩም ይገለጣል።
17
እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።
18
ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ ይህ ለመጭው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤
19
“ እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቷልና፤ ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቷል፤
20
ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”
21
ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤
22
ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል።
23
ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤ ዕድሜዬንም በዐጭሩ አስቀረው።
24
እኔም እንዲህ አልሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፤ ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።
25
አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።
26
እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።
27
አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።
28
የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤ ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”
← Chapter 101
Chapter 103 →