bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Numbers 29
Numbers 29
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
“ ‘በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩበት፤ ይህም የመለከት ድምፅ የምታሰሙበት ቀናችሁ ነው።
2
እንከን የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።
3
ከወይፈኑ ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራውም በግ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ፣ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት አቅርቡ፤
4
ከእያንዳንዱም ሰባት የበግ ጠቦት ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ።
5
ማስተስረያ እንዲሆናችሁም አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ በተጨማሪ አቅርቡ።
6
እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋር በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው።
7
“ ‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በዐሥረኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፤ ሥራም አትሥሩ።
8
ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፣ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።
9
ከወይፈኑ ጋር ለእህል ቍርባን የሚሆን የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ዱቄት አቅርቡ፤
10
ከሰባቱ የበግ ጠቦቶችም ከእያንዳንዳቸው ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ።
11
ማስተስረያ እንዲሆንም ለኀጢአት መሥዋዕት ከሚቀርበው እንዲሁም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ቀርቦ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
12
“ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም (ያህዌ) የሰባት ቀን በዓል አክብሩ።
13
ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ እንዲያሰኝ በእሳት አቅርቡ።
14
ከዐሥራ ሦስቱ ወይፈኖች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከሁለቱ አውራ በጎችም ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አቅርቡ፤
15
እንዲሁም ከዐሥራ አራቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አቅርቡ።
16
ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
17
“ ‘በሁለተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
18
ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር በተወሰነው ቍጥር መሠረት የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን አብራችሁ አቅርቡ።
19
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ አውራ ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
20
“ ‘በሦስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ አንድ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
21
ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አብራችሁ አቅርቡ።
22
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
23
“ ‘በአራተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
24
ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተደነገገው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።
25
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
26
“ ‘በአምስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
27
ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።
28
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
29
“ ‘በስድስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
30
ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።
31
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
32
“ ‘በሰባተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
33
ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።
34
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
35
“ ‘በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩ።
36
ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ቍርባን በእሳት አቅርቡ።
37
ከወይፈኑ፣ ከአውራ በጉና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።
38
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
39
“ ‘በስእለትና በበጎ ፈቃድ ከምታቀርቧቸው ቍርባኖች በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቍርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቍርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በተወሰኑት በዓሎቻችሁ ላይ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) አቅርቡ።’ ”
40
ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው።
← Chapter 28
Chapter 30 →