bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Numbers 21
Numbers 21
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ እስራኤል በአታሪም መንገድ መምጣቱን በሰማ ጊዜ በእስራኤላውያን ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ።
2
በዚያን ጊዜ እስራኤል፣ “ይህን ሕዝብ አሳልፈህ በእጃችን ከሰጠኸን ከተሞቻቸውን ፈጽሞ እንደመስሳለን” ሲል ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ተሳለ።
3
እግዚአብሔርም (ያህዌ) የእስራኤልን ልመና ሰምቶ ከነዓናውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰዎቹንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ከዚህ የተነሣም ስፍራው ሖርማ ተባለ።
4
እስራኤላውያን በኤዶም ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመንገድ ሳለ ትዕግሥቱ ዐለቀ፤
5
በእግዚአብሔርና (ኤሎሂም) በሙሴም ላይ ተነሥተው፣ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ! ውሃ የለ! ይህን የማይረባ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል” ሲሉ ተናገሩ።
6
በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) መርዘኛ እባቦች ሰደደባቸው፤ ሕዝቡን ነደፉ፤ ብዙ እስራኤላውያንም ሞቱ።
7
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥቶ፣ “ በእግዚአብሔርና (ያህዌ) በአንተ ላይ በመናገራችን በድለናል፤ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅልን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጸልይልን” አለ፤ ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ።
8
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “እባብ ሠርተህ በዕንጨት ላይ ስቀለው፤ የተነደፈውም ሁሉ ወደ እርሱ በማየት ይድናል” አለው።
9
ስለዚህ ሙሴ የናስ እባብ ሠርቶ በዕንጨት ላይ ሰቀለ፤ ከዚያም በእባብ የተነደፈ ማናቸውም ሰው ወደ ናሱ እባብ በተመለከተ ጊዜ ይድን ነበር።
10
እስራኤላውያን ተጓዙ፤ በኦቦትም ሰፈሩ፤
11
ከዚያም ከኦቦት ተነሥተው፣ በፀሓይ መውጫ ትይዩ ባለው ምድረ በዳ በዒዮዓባሪም ሰፈሩ።
12
ከዚያም ተጕዘው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ።
13
ከዚያም ተነሥተው እስከ አሞራውያን ግዛት በሚዘልቀው ምድረ በዳ ባለው በአርኖን አጠገብ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ወሰን ነው።
14
እንግዲህ በእግዚአብሔር (ያህዌ) የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በዚሁ የተነሣ ነው፤ “…በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ አርኖንና
15
ወደ ዔር የሚወስዱት በሞዓብ ድንበርም የሚገኙት የሸለቆች ተረተሮች።”
16
ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደ ተባለው የውሃ ጕድጓድ ጕዟቸውን ቀጠሉ።
17
ከዚያም እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፤ “አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ! እናንተም ዘምሩለት፤
18
ልዑላን ለቈፈሩት፣ የሕዝብ አለቆች በበትረ መንግሥታቸውና በበትሮቻቸው ላጐደጐዱት፣ የውሃ ጕድጓድ ዘምሩለት።” ከዚህ በኋላ ከምድረ በዳው ወደ መቴና ሄዱ፤
19
ከመቴና ወደ ነሃሊኤል፣ ከነሃሊኤልም ወደ ባሞት፣
20
ከባሞትም ፈስጋ ላይ ሆኖ ምድረ በዳው ቍልቍል ወደሚታይበት በሞዓብ ወደሚገኘው ሸለቆ ተጓዙ።
21
እስራኤል ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ የሚሉ መልእክተኞች ላከ፤
22
“በአገርህ ዐልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ ወደ የትኛውም ዕርሻ ሆነ የወይን አትክልት አንገባም፤ ወይም ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስም የንጉሡን አውራ ጐዳና አንለቅም።”
23
ሴዎን ግን እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዲያልፍ አልፈቀደም፤ ሰራዊቱን በሙሉ አሰባስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ወጣ፤ ያሀጽ እንደ ደረሰም ከእስራኤል ጋር ጦርነት ገጠመ።
24
እስራኤል ግን በሰይፍ መታው፤ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ድረስ ያለውንም ምድሩን ወሰደበት፤ ይሁን እንጂ የአሞናውያን ወሰን የተመሸገ ስለ ነበር ከያቦቅ አላለፈም።
25
እስራኤልም ሐሴቦንና በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች ጨምሮ የአሞራውያንን ከተሞች በሙሉ በመያዝ እዚያው ተቀመጠ።
26
ሐሴቦን የቀድሞውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድሩን የወሰደበት የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረች።
27
እንግዲህ ባለቅኔዎች እንደዚህ ያሉት ለዚህ ነው፤ “ወደ ሐሴቦን ኑ፣ እንደ ገና ትገንባ፤ የሴዎንም ከተማ ተመልሳ ትሠራ።
28
“እሳት ከሐሴቦን ወጣ፤ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ተንቦገቦገ፤ የሞዓብን ዔር፣ በአርኖን ከፍታዎች የሚኖሩትንም በላ።
29
ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ! የከሞስ ሕዝብ ሆይ፤ ተደመሰስህ! ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፣ ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ፣ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን አሳልፎ ሰጥቷል።
30
“እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”
31
ስለዚህም እስራኤል በአሞራውያን ምድር ተቀመጠ።
32
ሙሴ ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ከላከ በኋላ እስራኤላውያን በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አባረሯቸው።
33
ከዚያም ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ በመያዝ ሄዱ፤ የባሳን ንጉሥ ዐግና መላ ሰራዊቱም ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥሟቸው ወጡ።
34
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “እርሱን ከመላው ሰራዊቱና ከምድሩ ጋር በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን ሁሉ በእርሱም ላይ አድርግበት” አለው።
35
ስለዚህም እስራኤላውያን ዐግን ከልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋር አንድም ሳይቀሩ ሁሉንም ፈጇቸው፤ ምድሩንም ወረሱ።
← Chapter 20
Chapter 22 →