bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Nehemiah 7
Nehemiah 7
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ።
2
በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው።
3
ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያደርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።
4
ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር።
5
ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።
6
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ።
7
የተመለሱትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋር ነው። የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፦
8
ከፋሮስ ዘሮች 2,172
9
ከሰፋጥያስ ዘሮች 372
10
ከኤራ ዘሮች 652
11
ከኢያሱና ከኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,818
12
ከኤላም ዘሮች 1,254
13
ከዛቱዕ ዘሮች 845
14
ከዘካይ ዘሮች 760
15
ከቢንዊ ዘሮች 648
16
ከቤባይ ዘሮች 628
17
ከዓዝጋድ ዘሮች 2,322
18
ከአዶኒቃም ዘሮች 667
19
ከበጉዋይ ዘሮች 2,067
20
ከዓዲን ዘሮች 655
21
በሕዝቅያስ የትውልድ ሐረግ ከአጤር ዘሮች 98
22
ከሐሱም ዘሮች 328
23
ከቤሳይ ዘሮች 324
24
ከሐሪፍ ዘሮች 112
25
ከገባዖን ዘሮች 95
26
ከቤተ ልሔምና ከነጦፋ ሰዎች 188
27
ከዓናቶት ሰዎች 128
28
ከቤት አዝሞት ሰዎች 42
29
ከቂርያትይዓሪም፣ ከከፊራና ከብኤሮት ሰዎች 743
30
ከራማና ከጌባ ሰዎች 621
31
ከማክማስ ሰዎች 122
32
ከቤቴልና ከጋይ ሰዎች 123
33
ከሌላው ናባው ሰዎች 52
34
ከሌላው ኤላም ዘሮች 1,254
35
ከካሪም ዘሮች 320
36
ከኢያሪኮ ዘሮች 345
37
ከሎድ፣ ከሐዲድና ከኦኖም ዘሮች 721
38
ከሴናዓ ዘሮች 3,930
39
ካህናቱ፦ በኢያሱ ቤተ ሰብ መሥመር ከዮዳኤ ዘሮች 973
40
ከኢሜር ዘሮች 1,052
41
ከፋስኮር ዘሮች 1,247
42
ከካሪም ዘሮች 1,017
43
ሌዋውያኑ፦ በቀድምኤል በኩል በሆዳይዋ የትውልድ መሥመር የኢያሱ ዘሮች 74
44
መዘምራኑ፦ ከአሳፍ ዘሮች 148
45
በር ጠባቂዎቹ፦ ከሰሎም፣ ከአጤር፣ ከጤልሞን፣ ከዓቁብ፣ ከሐጢጣና ከሶባይ ዘሮች 138
46
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ ከሲሐ፣ ከሐሡፋ፣ ከጠብዖት ዘሮች፣
47
ከኬራስ፣ ከሲዓ፣ ከፋዶን፣
48
ከልባና፣ ከአጋባ፣ ከሰምላይ ዘሮች፣
49
ከሐናን፣ ከጌዴል፣ ከጋሐር ዘሮች፣
50
ከራያ፣ ከረአሶን፣ ከኔቆዳ ዘሮች፣
51
ከጋሴም፣ ከዖዛ፣ ከፋሴሐ ዘሮች፣
52
ከቤሳይ፣ ከምዑኒም፣ ከንፉሰሲም ዘሮች፣
53
ከበቅቡቅ፣ ከሐቀፋ፣ ከሐርሑር ዘሮች፣
54
ከበስሎት፣ ከምሒዳ፣ ከሐርሻ ዘሮች፣
55
ከቦርቆስ፣ ከሲሣራ፣ ከቴማ ዘሮች፣
56
ከንስያ፣ ከሐጢፋ ዘሮች።
57
የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬትና፣ የፍሩዳ ዘሮች፣
58
የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጊዴል ዘሮች፣
59
የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈከራት ዘሮች፣ የሐፂቦይምና የአሞን ዘሮች።
60
392
61
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የተመለሱ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦
62
የዳላያ፣ የጦብያ፣ የኔቆዳ ዘሮች 642
63
ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።
64
እነዚህ የየቤተ ሰቡ ትውልድ ሐረጋቸውን ከመዝገብ ለማግኘት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ።
65
ስለዚህም አገረ ገዥው በኡሪምና በቱሚም አገልግሎት የሚሰጥ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
66
የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤
67
ይህ 7,337 የወንድና የሴት አገልጋዮቻቸውን አይጨምርም፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው።
68
736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች ፣
69
435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው።
70
አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።
71
ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 የብር ምናን ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
72
የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 የብር ምናንና 67 አልባሰ ተክህኖ ነበር።
73
ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣
← Chapter 6
Chapter 8 →