bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Job 8
Job 8
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ሹሐዊውም በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤
2
“እንዲህ ያለውን ነገር የምትናገረው፣ ቃልህም እንደ ብርቱ ነፋስ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?
3
እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን? ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?
4
ልጆችህ በእርሱ ላይ ኀጢአት ሠርተው ከሆነ፣ ለኀጢአታቸው ቅጣት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል።
5
ነገር ግን አንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለከት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን ብትማፀን፣
6
ንጹሕና ቅን ብትሆን፣ እርሱ ስለ አንተ አሁኑኑ ይነሣል፤ ወደ ተገቢውም ስፍራህ ይመልስሃል።
7
ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
8
“የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፤ አባቶቻቸውም የደረሱበትን መርምረህ አግኝ፤
9
እኛ ትናንት ስለ ተወለድን አንዳች አናውቅምና፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው።
10
እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፣ ከልቦናቸውም ቃልን የሚያወጡ አይደሉምን?
11
ደንገል ረግረግ በሌለበት ስፍራ ይበቅላልን? ቄጠማስ ውሃ በሌለበት ይለመልማልን?
12
ገና በማደግ ላይ እያለ ሳይታጨድ፣ ከሌሎች ዕፀዋት ፈጥኖ ይደርቃል።
13
እግዚአብሔርን የሚረሱ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ አምላክ የለሽ ኑሮ የሚኖሩም ሁሉ ተስፋቸው ትጠፋለች።
14
መተማመኛው ቀጭን ክር፣ ድጋፉም የሸረሪት ድር ነው።
15
ድሩ ላይ ቢደገፍ ይበጠስበታል፤ አጥብቆም ቢይዘው አይጸናም።
16
ውሃ እንደ ጠገበ ተክል፣ ፀሓይ እየሞቀው፣ ቅርንጫፉን ሁሉ በአትክልቱ ስፍራ ላይ ይዘረጋል።
17
ሥሩን በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጥማል፤ በዐለትም መካከል ስፍራ ያበጃል።
18
ከስፍራው ሲወገድ ግን፣ ያ ቦታ ‘አይቼህ አላውቅም’ ብሎ ይክደዋል።
19
እነሆ፤ ሕይወቱ በዚህ ያከትማል፤ ሌሎች አትክልትም ከመሬት ይበቅላሉ።
20
“እነሆ፤ እግዚአብሔር እንከን የሌለበትን ሰው አይጥልም፤ የክፉዎችንም እጅ አያበረታም፤
21
እንደ ገና አፍህን በሣቅ፤ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል።
22
ጠላቶችህ ኀፍረት ይለብሳሉ፤ የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።”
← Chapter 7
Chapter 9 →