bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Jeremiah 47
Jeremiah 47
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ፈርዖን ጋዛን ድል ከማድረጉ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
2
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፤ ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤ አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣ ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል። ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤
3
ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣ ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣ አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤ እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።
4
ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ ቀኑ ደርሷልና። እግዚአብሔር በከፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋ ተነሥቷል።
5
ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፤ አስቀሎና አፏን ትይዛለች። በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ቅሬታዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?
6
“ ‘ የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፤ የማታርፈው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤ ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።
7
ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣ እንዲወጋ ሲያዝዘው፣ እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣ እንዴት ማረፍ ይችላል?”
← Chapter 46
Chapter 48 →