bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 64
Isaiah 64
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
አቤቱ፤ ሰማያትን ቀድደህ ምነው በወረድህ! ምነዋ ተራሮች በፊትህ በተናወጡ!
2
እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ ውሃንም እንደሚያፈላ፣ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤ መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ።
3
እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣ አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።
4
ከጥንት ጀምሮ፣ በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣ እንደ አንተ ያለውን አምላክ ያየ ዐይን፣ ያደመጠ ጆሮ ፈጽሞ አልነበረም።
5
በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣ መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤ እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣ እነሆ፤ ተቈጣህ፤ ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን?
6
ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
7
ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤ አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤ ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤ ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል።
8
ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤
9
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤ ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤ እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤ ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና።
10
የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆኑ፤ ጽዮን ራሷ እንኳ ምድረ በዳ፣ ኢየሩሳሌምም የተፈታች ሆናለች።
11
አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣ በእሳት ተቃጥሏል፤ ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል።
12
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ አትመለስምን? ዝም ብለህ ከልክ በላይ ትቀጣናለህን?
← Chapter 63
Chapter 65 →