bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 52
Isaiah 52
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም።
2
ትቢያሽን አራግፊ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤ ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ የዐንገትሽን የእስራት ሰንሰለት አውልቀሽ ጣዪ።
3
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ ያለ ገንዘብ ትቤዣላችሁ።”
4
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመጀመሪያ ሕዝቤ ይኖር ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በኋላም አሦር ያለ ምክንያት አስጨንቆ ገዛው።
5
“አሁን እዚህ ምን አለኝ?” ይላል እግዚአብሔር ፤ “ሕዝቤ ያለ ምክንያት ተወስዷል፤ የገዟቸው ተሣልቀውባቸዋል” ይላል እግዚአብሔር ። “ቀኑን ሙሉ፣ ስሜ ያለ ማቋረጥ ይሰደባል።
6
ስለዚህ ሕዝቤ ስሜን ያውቃል፤ በዚያ ቀንም፣ አስቀድሜ የተናገርሁ እኔ መሆኔን ይረዳል፤ እነሆ፤ እኔው ነኝ።”
7
በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራች ይዘው የሚመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሧል” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።
8
ስሚ፤ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤ በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ። እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣ በዐይኖቻቸው ያያሉ።
9
እናንት የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷል፤ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷልና።
10
እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ የተቀደሰ ክንዱን ይገልጣል፤ በምድር ዳርቻዎች ያሉ ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
11
እናንት የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣ ተለዩ፤ ተለዩ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስ ነገር አትንኩ፤ ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ።
12
ሆኖም በችኰላ አትወጡም፤ ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ እግዚአብሔር ፊት ፊታችሁ ይሄዳል፤ የእስራኤል አምላክ ደጀን ይሆናችኋል።
13
እነሆ፤ ባሪያዬ የሚያከናውነው በማስተዋል ነው፤ ገናና ይሆናል፤ ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግ ይከብራልም።
14
ብዙዎች በእርሱ እስኪደነግጡ ድረስ፣ መልኩ ከማንም ሰው ተለየ፤ ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ።
15
ስለዚህ ብዙ መንግሥታትን ያስደንቃል፤ በእርሱ ምክንያት ነገሥታት አፋቸውን ይይዛሉ፤ ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ ያልሰሙትን ያስተውላሉ።
← Chapter 51
Chapter 53 →