bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 28
Isaiah 28
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፣ በለመለመ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት ለሆነች ጠውላጋ አበባ፣ የወይን ጠጅ ለዘራቸው መኵራሪያ ለሆነች፣ ለዚያች ከተማ ወዮላት!
2
እነሆ፤ ጌታ ኀያልና ብርቱ የሆነ ነገር አለው፤ ይህም እንደ በረዶ ወጀብ፣ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስ፣ እንደ ኀይለኛ ማዕበል፣ እንደ ከባድ ዝናብ፣ በኀይል ወደ ምድር ይጥላታል።
3
የኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል፣ በእግር ይረገጣል።
4
በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋት ወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።
5
በዚያን ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፣ ለተረፈው ሕዝቡ፣ የክብር ዘውድ፣ የውበትም አክሊል ይሆናል።
6
እርሱም በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጠው፣ የፍትሕ መንፈስ፣ ጦርን ከከተማዪቱ በር ላይ ለሚመልሱም፣ የኀይል ምንጭ ይሆናል።
7
እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤ በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤ ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገዳገዱ፤ በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤ በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤ ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ።
8
የማእድ ገበታቸው ሁሉ በትፋት ተሞልቷል፤ ከትውኪያም የጸዳ ቦታ የለም።
9
እነርሱም እንዲህ ይላሉ፤ “የሚያስተምረው ማንን ነው? መልእክቱን የሚያብራራውስ ለማን ነው? ወተት ለተዉት ሕፃናት? ወይስ ጡት ለጣሉት?
10
በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፤ በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤ እዚህ ጥቂት፣ እዚያ ጥቂት ነውና።”
11
እንግዲያማ እግዚአብሔር ፣ በባዕድ ልሳን በእንግዳ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል።
12
እርሱ፣ “ይህች የዕረፍት ቦታ ናት፤ የደከመው ይረፍ፤ ይህች የእፎይታ ቦታ ናት” ያለው ለማን ነበር? እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም።
13
ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፤ በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤ እዚህ ጥቂት እዚያ ጥቂት ይሆንባቸዋል። ይህ የሚሆንባቸው ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲቈስሉና በወጥመድ እንዲያዙ፣ እንዲማረኩም ነው።
14
ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ፣ እናንት ፌዘኞች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
15
እናንት፣ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል፤ ከሲኦልም ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ውሸትን መጠጊያችን፣ ሐሰትን መደበቂያችን አድርገናል፤ ታላቅ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ ሊነካን አይችልም” በማለት ታብያችኋል።
16
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የተፈተነ ድንጋይ፣ የመሠረት ድንጋይ፣ ለጽኑ መሠረት የሚሆን የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣ በጽዮን አስቀምጣለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
17
ፍትሕን የመለኪያ ገመድ፣ ጽድቅንም ቱንቢ አደርጋለሁ፤ ውሸት መጠጊያችሁን የበረዶ ዝናብ ይጠራርገዋል፤ መደበቂያችሁንም ውሃ ያጥለቀልቀዋል።
18
ከሞት ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይሻራል፤ ከሲኦልም ጋር ያደረጋችሁት ስምምነት ይፈርሳል፤ ታላቁ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ እናንተም ትጠራረጋላችሁ።
19
በመጣ ቍጥር ይዟችሁ ይሄዳል፤ ማለዳ ማለዳ፣ በቀንና በሌሊትም ይጠራርጋል።” ይህን ቃል ብታስተውሉ፣ ሽብር በሽብር በሆነ ነበር።
20
እግር ዘርግቶ እንዳይተኛ ዐልጋው ዐጭር ነው፤ ሰውነትንም ለመሸፋፈን ብርድ ልብሱ ጠባብ ነው።
21
እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣ በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።
22
እንግዲህ ፌዛችሁን አቁሙ፤ አለዚያ እስራታችሁ ይጸናባችኋል፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፣ መላውን ምድር ለማጥፋት ያወጀውን ዐዋጅ ሰምቻለሁ።
23
አድምጡ ድምፄን ስሙ፤ አስተውሉ ቃሌንም ስሙ።
24
ገበሬ ሊዘራ መሬቱን ሲያዘጋጅ ያለ ማቋረጥ ያርሳልን? ጓሉን ሲከሰክስ፣ ዐፈሩን ሲያለሰልስ ይከርማልን?
25
ዕርሻውን አስተካክሎ፣ ጥቍር አዝሙድና ከሙን አይዘራምን? ስንዴውንስ በትልሙ ፣ ገብሱን በተገቢ ቦታው፣ አጃውንም በተመደበው ስፍራ አይዘራምን?
26
አምላኩ ያስተምረዋል፤ ትክክለኛውንም መንገድ ያሳየዋል።
27
ጥቍር አዝሙድ በመውቂያ መሣሪያ አይወቃም፤ ከሙን የሠረገላ መንኰራኵር አይሄድበትም፤ ጥቍር አዝሙድ በበትር፣ ከሙንም በዘንግ ይወቃል።
28
እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ ስለዚህ አንድ ሰው ለዘላለም እህል ሲወቃ አይኖርም። የመውቂያውን መንኰራኵር ቢያኼድበትም፣ ፈረሶቹ አይደፈጥጡትም።
29
ይህ ሁሉ የሚሆነው በምክሩ ድንቅ፣ በጥበቡ ታላቅ ከሆነው፣ ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
← Chapter 27
Chapter 29 →