bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 25
Isaiah 25
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፣ ድንቅ ነገር፣ በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና።
2
ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤ የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤ የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤ ተመልሳም አትሠራም።
3
ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል።
4
ለድኻ መጠጊያ፣ በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣ ከማዕበል መሸሸጊያ፣ ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል። የጨካኞች እስትንፋስ፣ ከግድግዳ ጋር እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤
5
እንደ ምድረ በዳም ትኵሳት ነው። የባዕድን ጩኸት እረጭ ታደርጋለህ፤ ትኵሳት በደመና ጥላ እንደሚበርድ፣ የጨካኞችም ዝማሬም እንዲሁ ጸጥ ይላል።
6
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።
7
በዚህም ተራራ ላይ፣ በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤
8
ሞትንም ለዘላለም ይውጣል። ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ውርደት ከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሯልና።
9
በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤ “እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤ በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”
10
የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤ ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋር እንደሚረገጥ፣ ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል።
11
ዋናተኛ ሲዋኝ እጁን እንደሚዘረጋ፣ በውስጡ ሆነው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ ጌታ በእጃቸው ተንኰል ሳይታለል፣ ትዕቢታቸውን ያዋርዳል።
12
ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤ ወደ ታች ያወርደዋል፤ ወደ ምድር አውርዶም ትቢያ ላይ ይጥለዋል።
← Chapter 24
Chapter 26 →