bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Isaiah 23
Isaiah 23
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ! ጢሮስ ተደምስሳለችና፣ ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች። ከቆጵሮስ ምድር፣ ዜናው ወጥቶላቸዋል።
2
እናንት የባሕር ተጓዦች ያበለጠጓችሁ፣ በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ የሲዶና ነጋዴዎችም ጸጥ በሉ።
3
በታላላቅ ውሆች ላይ፣ ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤ የአባይ መከር ገቢዋ ነበር፤ እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች።
4
አንቺ ሲዶና ሆይ፤ አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፤ ዕፈሪ፤ ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሏልና።
5
ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣ በግብፅ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።
6
እናንት በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤ ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤
7
እግሮቿ ሩቅ አገር የወሰዷት፣ በዚያም እንድትሰፍር ያደረጓት፣ ጥንታዊቷ የድሮ ከተማ፣ የተድላ ከተማችሁ ይህች ናትን?
8
አክሊል በምታቀዳጀዋ፣ ነጋዴዎቿ መሳፍንት በሆኑ፣ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፣ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?
9
የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣ በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኗል።
10
የተርሴስ ልጅ ሆይ፤ ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምና እንደ አባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ።
11
እግዚአብሔር እጁን በባሕር ላይ ዘረጋ፤ መንግሥታቷንም አስደነገጠ፤ የከነዓንም ምሽጎች እንዲፈርሱ፣ ትእዛዝ ሰጠ፤
12
እንዲህም አለ፤ “አንቺ የተቀጠቀጥሽ የሲዶን ድንግል ሆይ፤ ከእንግዲህ ደስ አይበልሽ! “ተነሺ ወደ ቆጵሮስ ተሻገሪ፤ በዚያም እንኳ ሰላም አታገኚም።”
13
እነሆ፤ የባቢሎናውያንን ምድር ተመልከቱ፤ ሕዝቡ ከንቱ ሆኗል። አሦራውያን የምድረ በዳ አራዊት መፈንጪያ አደረጓት፤ የግንብ ማማቸውን ሠሩባት፤ ምሽጎቿን አወደሙ፤ የፍርስራሽ ክምር አደረጓት።
14
እናንት የተርሴስ መርከቦች፣ ዋይ በሉ፤ ምሽጋችሁ ፈርሷል።
15
በዚያ ጊዜ ጢሮስ፣ የአንድ ንጉሥ የሕይወት ዘመን ያህል፣ ለሰባ ዓመታት ትረሳለች። ከሰባ ዓመት በኋላ ግን፣ ስለ ጋለሞታዪቱ የተዘፈነው በጢሮስ ላይ ይሆናል፤
16
“አንች የተረሳሽ ጋለሞታ፤ በገና አንሺ፤ በከተማዪቱ ውስጥ ዙሪ፤ እንድትታወሺም፣ በገናሽን አሳምረሽ ምቺ፤ ብዙ ዘፈን ዝፈኚ።”
17
ሰባው ዓመት ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞው የግልሙትና ሥራዋ ተመልሳ፣ በምድር ላይ ካሉት የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር በንግዷ ትገለሙታለች።
18
ያም ሆኖ ትርፏና ያገኘችው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ አይከማችም፤ አይጠራቀምም። ትርፏም በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩት የተትረፈረፈ ምግብና ጥሩ ልብስ ይሆናል።
← Chapter 22
Chapter 24 →