bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Hosea 7
Hosea 7
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።
2
ነገር ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ፣ እነርሱ አይገነዘቡም፤ ኀጢአታቸው ከብቧቸዋል፤ ሁልጊዜም በፊቴ ናቸው።
3
“ንጉሡን በክፋታቸው፣ አለቆችንም በሐሰታቸው ያስደስታሉ።
4
ሊጡ ቦክቶ ኩፍ እንደሚል፣ ዳቦ ጋጋሪው እሳት መቈስቈስ እስከማያስፈልገው ድረስ፣ እንደሚነድድ ምድጃ፣ ሁሉም አመንዝራ ናቸው።
5
በንጉሣችን የበዓል ቀን፣ አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤ እርሱም ከፌዘኞች ጋር ተባበረ።
6
ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤ በተንኰል ይቀርቡታል፤ ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤ እንደሚነድድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል።
7
ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ ገዦቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።
8
“ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው።
9
እንግዶች ጕልበቱን በዘበዙ፤ እርሱ ግን አላስተዋለም። ጠጕሩም ሽበት አወጣ፤ እርሱ ግን ልብ አላለም።
10
የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እርሱንም አልፈለገም።
11
“ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣ አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤ አንድ ጊዜ ወደ ግብፅ ይጣራል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።
12
ሲበርሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼ አወርዳቸዋለሁ፤ ስለ ክፉ ሥራቸውም፣ በጕባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።
13
ወዮ ለእነርሱ፤ ከእኔ ርቀው ሄደዋልና! ጥፋት ይምጣባቸው! በእኔ ላይ ዐምፀዋልና። ልታደጋቸው ፈለግሁ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።
14
ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፤ ነገር ግን በዐልጋቸው ላይ ሆነው ያለቅሳሉ። ስለ እህልና ስለ አዲስ የወይን ጠጅ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን ከእኔ ዘወር ብለዋል።
15
እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐደሙብኝ።
16
ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው፤ መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር፣ መዘባበቻ ይሆናሉ።”
← Chapter 6
Chapter 8 →