bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Hosea 11
Hosea 11
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
“እስራኤል ገና ሕፃን ሳለ ወደድሁት፤ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት።
2
እስራኤል ግን አብዝቼ በጠራኋቸው ቍጥር፣ አብዝተው ከእኔ ራቁ፤ ለበኣል አማልክት ሠዉ፤ ለምስሎችም ዐጠኑ።
3
ኤፍሬምን እጁን ይዤ፣ እንዲራመድ ያስተማርሁት እኔ ነበርሁ፤ ነገር ግን የፈወስኋቸው እኔ እንደ ሆንሁ፣ እነርሱ አላስተዋሉም።
4
በሰው የርኅራኄ ገመድ፣ በፍቅርም ሰንሰለት ሳብኋቸው፤ ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ አነሣሁላቸው፤ ዝቅ ብዬም መገብኋቸው።
5
“ታዲያ ንስሓ መግባትን እንቢ በማለታቸው፣ ወደ ግብፅ አይመለሱምን? አሦርስ አይገዛቸውምን?
6
በከተሞቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዛል፤ የበሮቻቸውን መወርወሪያ ይቈርጣል፤ ስለ ክፉ ዕቅዳቸውም ይደመስሳቸዋል።
7
ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤ ወደ ልዑል ቢጣሩም፣ በምንም ዐይነት አያከብራቸውም።
8
“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።
9
የቍጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤ ተመልሼም ኤፍሬምን አላጠፋም፤ እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣ ሰው አይደለሁምና፣ በቍጣ አልመጣም።
10
እግዚአብሔርን ይከተላሉ፤ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ እርሱ ሲያገሣ፣ ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።
11
እንደ ወፍ ከግብፅ፣ እንደ ርግብ ከአሦር፣ እየበረሩ ይመጣሉ፤ እኔም በቤታቸው አኖራቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር ።
12
ኤፍሬም በሐሰት፣ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤ ይሁዳ ለአምላክ የማይገዛ፣ የታመነውን ቅዱሱን የሚቃወም ነው።
← Chapter 10
Chapter 12 →