bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Ezekiel 30
Ezekiel 30
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
2
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤ “ወዮ ለዚያ ቀን!”
3
ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደመና ቀን፣ ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።
4
በግብፅ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤ በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል። የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ ሀብቷ ይወሰዳል፤ መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።
5
ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ልድያና መላው ዐረብ፣ ሊብያና የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብፅ ጋር በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።
6
“ ‘ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የግብፅ ተባባሪዎች ይወድቃሉ። የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል። ከሚግዶል እስከ አስዋን፣ በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ።
7
በባድማ መሬቶች መካከል፣ ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞቻቸውም፣ ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።
8
በግብፅ ላይ እሳት ስጭር፣ ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቅቁ፣ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
9
“ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ተዘልላ ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብፅ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በርግጥ ይመጣልና።
10
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፣ ስፍር ቍጥር የሌለውን የግብፅን ሕዝብ እደመስሳለሁ።
11
ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣ ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤ ሰይፋቸውን በግብፅ ላይ ይመዝዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤
12
የአባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤ ምድሪቱን ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ፤ በባዕዳን እጅ፣ ምድሪቷንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።
13
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጣዖታትን አጠፋለሁ፤ በሜምፊስ ያሉትን ምስሎች እደመስሳለሁ። ከእንግዲህ በግብፅ ገዥ አይኖርም፣ በምድሪቱም ላይ ፍርሀት እሰዳለሁ።
14
ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤ በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤ በቴብስ ላይ ቅጣት አመጣለሁ።
15
የግብፅ ምሽግ በሆነችው፣ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ።
16
በግብፅ ላይ እሳት አነድዳለሁ፤ ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤ ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤ ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።
17
የሄልዮቱና የቡባስቱ ጕልማሶች፣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ከተሞቹ ራሳቸውም ይማረካሉ።
18
የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል። በደመና ትሸፈናለች፤ መንደሮቿም ይማረካሉ።
19
ስለዚህ በግብፅ ላይ ቅጣቴን አመጣለሁ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
20
በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር በሰባተኛው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
21
“የሰው ልጅ ሆይ፤ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ ይፈወስ ዘንድ ክንዱ አልተጠገነም፤ ወይም ሰይፍ መያዝ ይችል ዘንድ እጁ በመቃ አልታሰረም።
22
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነሥቻለሁ፤ ደኅናውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።
23
ግብፃውያንን በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።
24
የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።
25
የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንድ ግን ይዝላል፤ ሰይፌን በባቢሎን ንጉሥ እጅ ሳስይዝ፣ እርሱም ሲነቀንቀው፣ ያኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።
26
በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
← Chapter 29
Chapter 31 →