bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Exodus 15
Exodus 15
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘመሩ፤ “ከፍ ከፍ ብሎ ከብሯልና፣ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏልና።
2
“ እግዚአብሔር (ያህ) ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ (ኤሎሂም) ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
3
እግዚአብሔር (ያህዌ) ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
4
የፈርዖንን ሠረገሎችና ሰራዊት፣ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ ምርጥ የሆኑት የፈርዖን ሹማምት፣ ቀይ ባሕር ውስጥ ሰጠሙ።
5
ቀላያትንም ለበሱ፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረዱ።
6
አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ቀኝ እጅህ በግርማ ከበረ፤ አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ቀኝ እጅህ ጠላትን አደቀቀ።
7
“በግርማህ ታላቅነት፣ የተቃወሙህን ጣልኻቸው፤ ቍጣህን ሰደድህ፤ እንደ ገለባም በላቸው።
8
በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ ውሆች ተቈለሉ፤ ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።
9
ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፤ እማርካቸዋለሁ፤ ምርኮን እካፈላለሁ፤ ነፍሴ በእነርሱ ትጠግባለች፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ትደመስሳቸዋለች አለ።’
10
አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤ በኀያላን ውሆች፣ እንደ ብረት ሰጠሙ።
11
አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ከአማልክት መካከል፣ እንደ አንተ ማን አለ? በቅድስናው የከበረ፣ በክብሩ የሚያስፈራ፣ ድንቆችን የሚያደርግ፣ እንደ አንተ ማን አለ?
12
“ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።
13
በማይለወጠው ፍቅርህ፣ የተቤዥሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤ እነርሱን በብርታትህ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ።
14
አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤ የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል።
15
የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤ የሞአብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤ የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ።
16
አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠኻቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
17
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ማደሪያህ እንዲሆን በሠራኸው ስፍራ፣ ጌታ (አዶናይ) ሆይ፤ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ፣ ታመጣቸዋለህ፤ ትተክላቸዋለህም።
18
“ እግዚአብሔር (ያህዌ) ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”
19
የፈርዖን ፈረሶች፣ ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) የባሕሩን ውሃ በላያቸው ላይ መለሰባቸው፤ እስራኤላውያን ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተሻገሩ።
20
ከዚያም የአሮን እኅት ነቢዪቱ ማርያም ከበሮዋን አንሥታ ያዘች፤ የቀሩትም ሴቶች ሁሉ ከበሮ ይዘው እያሸበሸቡ ተከተሏት።
21
ማርያምም፣ “ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏል፤ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘምሩ፤ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏልና” እያለች ዘመረችላቸው።
22
ከዚያም ሙሴ እስራኤልን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ፤ ለሦስት ቀናት ውሃ ሳያገኙም በምድረ በዳ ተጓዙ።
23
ማራ በደረሱ ጊዜ ውሃው መራራ ስለ ነበር ሊጠጡት አልቻሉም፤ ቦታው ማራ ተብሎ የተጠራውም ከዚህ የተነሣ ነው።
24
ሕዝቡም በሙሴ ላይ በማጕረምረም፣ “ምን እንጠጣ?” አሉ።
25
ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጮኸ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) አንዲት ዛፍ አሳየው፤ ዕንጨቷንም ወደ ውሃው ጣላት፤ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ። በዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሕግና ሥርዐት አበጀላቸው፤ በዚያም ስፍራ ፈተናቸው።
26
እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር (ያህዌ) ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝና።”
27
ከዚያም ዐሥራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ወዳሉበት ወደ ኤሊም መጡ፤ እነርሱም በውሃው አጠገብ በዚያ ሰፈሩ።
← Chapter 14
Chapter 16 →