bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
Esther 6
Esther 6
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
በዚያች ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ መተኛት አልቻለም። ስለዚህ በዘመነ መንግሥቱ የተመዘገበው የታሪክ መጽሐፍ ቀርቦ እንዲነበብለት አዘዘ።
2
በዚያም በሩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ የጦር አዛዦች ሁለቱ፣ ገበታና ታራ ንጉሥ ጠረክሲስን ለመግደል አሢረው እንደ ነበርና ይህንም መርዶክዮስ እንደ ተናገረ ተጽፎ ተገኘ።
3
ንጉሡም፣ “ታዲያ ይህን በማድረጉ መርዶክዮስ ያገኘው ክብርና ማዕረግ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። የቅርብ አገልጋዮቹም፣ “ምንም አልተደረገለትም” ብለው መለሱ።
4
ንጉሡም፣ “በአደባባዩ ማን አለ?” ሲል ጠየቀ። በዚህ ጊዜ ሐማ በተከለው ዕንጨት ላይ መርዶክዮስ ይሰቀል ዘንድ ለንጉሡ ለመናገር በውጭ በኩል ወደሚገኘው የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ገና መድረሱ ነበር።
5
የቅርብ አገልጋዮቹም፣ “እነሆ፤ ሐማ በአደባባዩ ቆሟል” አሉት። ንጉሡም፣ “ግባ በሉት” ብሎ አዘዘ።
6
ሐማ በገባ ጊዜ ንጉሡ፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለወደደው ሰው ምን ሊደረግለት ይገባል?” ሲል ጠየቀው። በዚህ ጊዜ ሐማ፣ “ንጉሡ ከእኔ ይልቅ የሚያከብረው ማን አለ?” ሲል በልቡ ዐሰበ።
7
ስለዚህ ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው፣
8
ንጉሡ የሚጐናጸፈው ልብሰ መንግሥት፣ ንጉሡም የሚቀመጥበትና የንጉሡን ዘውድ በራሱ ላይ ያደረገ ፈረስ ይምጣለት።
9
ከዚያም ልብሱና ፈረሱ እጅግ ከከበሩት ከንጉሡ ልዑላን መሳፍንት በአንዱ እጅ ይሰጥለት። ንጉሡ ሊያከብረው የወደደውን ሰው ያልብሱት፤ በፈረሱም ላይ አስቀመጠውም በከተማዪቱ ዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመሩ፣ ‘ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ይህ ተደርጎለታል’ ይበሉ።”
10
ንጉሡም ሐማን፣ “በል ፈጥነህ ሂድ፤ ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፤ በንጉሡ በር ላይ ለሚቀመጠው ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስም ልክ እንዳልኸው አድርግለት፤ ከተናገርኸውም አንዳች ነገር እንዳይጐድል” ሲል አዘዘው።
11
ስለዚህ ሐማ ልብሱንና ፈረሱን ወስዶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ በዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመራም፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ይህ ተደርጎለታል” እያለ በፊቱ ያውጅ ነበር።
12
ከዚያም በኋላ መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ በር ተመለሰ፤ ሐማ ግን ዐዝኖና ራሱን ተከናንቦ በጥድፊያ ወደ ቤቱ ሄደ።
13
የደረሰበትንም ሁሉ ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ነገራቸው። አማካሪዎቹና ሚስቱ ዞሳራም፣ “በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ዘሩ ከአይሁድ ወገን ከሆነ፣ ልትቋቋመው አትችልም፤ ያለ ጥርጥር ትጠፋለህ” አሉት።
14
ከእርሱ ጋር በመነጋገር ላይ ሳሉ፣ የንጉሡ ጃንደረቦች ደርሰው ሐማን አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ አጣደፉት።
← Chapter 5
Chapter 7 →