bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Chronicles 22
2 Chronicles 22
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ከዐረቦች ጋር ወደ ሰፈር የመጡት ወራሪዎች፣ ታላላቅ ወንድሞቹን ሁሉ ገድለዋቸው ስለ ነበር፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ የኢዮሆራምን የመጨረሻ ልጅ አካዝያስን በአባቱ ምትክ አነገሡት። ስለዚህ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሆራም ልጅ አካዝያስ መግዛት ጀመረ።
2
አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የዘንበሪ የልጅ ልጅ ነበረች።
3
እናቱ ክፋትን እንዲያደርግ ትመክረው ስለ ነበር፣ እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ።
4
ከአባቱ ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት አማካሪዎቹ በመሆን ወደ ጥፋት ስለ መሩት፣ የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።
5
እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን ለመውጋት ወደ ሬማት ገለዓድ በሄደ ጊዜ፣ የእነዚህኑ ሰዎች ምክር ተከትሎ ከኢዮራም ጋር አብሮት ሄደ፣ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።
6
ስለዚህ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር ባደረገው ጦርነት ሬማት ላይ ከደረሰበት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በመቍሰሉም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሆራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።
7
አካዝያስ ኢዮራምን ለመጠየቅ መሄዱን፣ እግዚአብሔር ለአካዝያስ መውደቅ ምክንያት አደረገው፤ አካዝያስ እንደ ደረሰም የናሜሲን ልጅ ኢዩን ለመቀበል ከኢዮራም ጋር ወጣ፤ ኢዩም የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የቀባው ሰው ነበር።
8
ኢዩ በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድ በሚፈጽምበት ጊዜ፣ አካዝያስን ያጅቡ የነበሩትን የይሁዳን መሳፍንትና የዘመዶቹን ወንዶች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።
9
ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ የእርሱም ሰዎች አካዝያስን በሰማርያ ከተደበቀበት አግኝተው ያዙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት። “ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት። ስለዚህ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዝ ዘንድ የሚችል ሰው አልነበረም።
10
የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ፣ የይሁዳን ንጉሣውያን ቤተ ሰብ በሙሉ አጠፋች፤
11
የንጉሥ ኢዮሆራም ልጅ ዮሳቤት ግን፣ ከሚገደሉት መሳፍንት መካከል ኢዮአስን ደብቃ ወሰደችው፣ ከሞግዚቱም ጋር በእልፍኝ ሸሸገችው። የኢዮሆራም ልጅ የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት፣ የአካዝያስ እኅት በመሆኗ፣ ሕፃኑን የደበቀችው ጎቶልያ እንዳትገድለው ነበር።
12
እርሱም ጎቶልያ ምድሪቱን በገዛችበት ጊዜ ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተደብቆ ስድስት ዓመት አብሯቸው ኖረ።
← Chapter 21
Chapter 23 →