bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Chronicles 17
2 Chronicles 17
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ልጁ ኢዮሣፍጥ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በእስራኤል ላይ በረታ።
2
እርሱም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር አኖረ፤ እንዲሁም በይሁዳ ምድርና አባቱ አሳ በያዛቸው በኤፍሬም መንደሮች ዘበኞች አስቀመጠ።
3
በለጋነት ዕድሜው አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ስለ ሄደ፣ እግዚአብሔር ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበር፤ የበኣልንም አማልክት አልጠየቀም፤
4
ነገር ግን ከእስራኤል ድርጊት ይልቅ፣ የአባቱን ፈለገ፤ ትእዛዞቹንም ተከተለ።
5
እግዚአብሔርም መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ መላው ይሁዳም ስጦታ አመጣለት፤ ከዚህ የተነሣም ታላቅ ብልጽግናና ክብር አገኘ።
6
ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ የጸና ነበር፤ እንደዚሁም ማምለኪያ ኰረብታዎችንና የአሼራ ዐምዶችን ከይሁዳ አስወገደ።
7
በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ ሹማምቱን፣ ማለትም ቤን ኀይልን፣ አብድያስን፣ ዘካርያስን፣ ናትናኤልንና ሚካያን ላካቸው።
8
ከእነዚህም ጋር ጥቂት ሌዋውያን ነበሩ፤ ስማቸውም፦ ሸማያ፣ ነታንያ፣ ዝባድያ፣ አሣሄል፣ ሰሚራሞት፣ ዮናትን፣ አዶንያስ፣ ጦብያና ጦባዶንያ ነበር። ካህናቱ ደግሞ ኢሊሳማና ኢዮራም ነበሩ።
9
እነርሱም የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በመሄድ በይሁዳ ሁሉ ላለው ሕዝብ አስተማሩ፤ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመዘዋወርም ሕዝቡን አስተማሩ።
10
በይሁዳ ዙሪያ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ስለ ወደቀባቸው ኢዮሣፍጥን አልተዋጉትም።
11
ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።
12
ኢዮሣፍጥም እያየለ ሄደ፤ በይሁዳም ምሽጎችና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች ሠራ።
13
በይሁዳም ከተሞች እጅግ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ነበረው። ደግሞም በቂ ልምድ ያላቸውን ተዋጊዎች በኢየሩሳሌም አስቀመጠ።
14
እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ጋር፤
15
ከእርሱ ቀጥሎም አዛዡ የሆሐናን ከሁለት መቶ ሰማንያ ሺሕ ጋር፤
16
ከዚያ ቀጥሎም ለእግዚአብሔር አገልግሎት በፈቃደኝነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ጋር፤
17
ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺሕ ሰዎች ጋር፤
18
ቀጥሎም ዮዛባት ለጦርነት ዝግጁ ከሆኑ ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ሰዎች ጋር፤
19
እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።
← Chapter 16
Chapter 18 →