bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
2 Chronicles 15
2 Chronicles 15
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ መጣ።
2
እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል።
3
እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል።
4
በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው።
5
በዚያን ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም።
6
እግዚአብሔር በተለያየ መከራ ያስጨንቃቸው ስለ ነበር፣ አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት፣ አንዱም ከተማ በሌላው ከተማ ይደመሰስ ነበር።
7
እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”
8
አሳ ይህን ቃልና የነቢዩን የዖዴድን ልጅ የዓዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ በረታ። ከመላው ይሁዳና ከብንያም ምድር፣ በኤፍሬምም ኰረብታዎች ላይ ከያዛቸው ከተሞች አስጸያፊዎቹን ጣዖታት አስወገደ። ከእግዚአብሔር መቅደስ ሰበሰብ ፊት ለፊት የነበረውንም የእግዚአብሔር መሠዊያ ዐደሰ።
9
አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን ባዩ ጊዜ፣ ከእስራኤል ብዙ ሰዎች እርሱን ተጠግተው ነበር፤ እርሱም ይሁዳንና ብንያምን እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ።
10
እነርሱም በአሳ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
11
በዚያን ጊዜ በምርኮ ካመጡት ውስጥ ሰባት መቶ በሬ፣ ሰባት ሺሕ በግና ፍየል ለእግዚአብሔር ሠዉ።
12
የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ።
13
የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሁሉ ግን፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል አደረጉ።
14
ይህንም በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ ለእግዚአብሔር ማሉ።
15
በፍጹም ልባቸው ስለማሉም የይሁዳ ሕዝብ በመሐላው ደስ ተሰኙ። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው።
16
እንዲሁም ንጉሥ አሳ አያቱን ማዓካን ለአስጸያፊዋ የአሼራ ጣዖት ዐምድ ስላቆመች ከእቴጌነት ክብሯ ሻራት። አሳም ዐምዱን ቈርጦ በመሰባበር በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው።
17
ምንም እንኳ ማምለኪያ ኰረብታዎችን ሙሉ በሙሉ ከእስራኤል ባያስወግድም፣ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፈጽሞ ለእግዚአብሔር የተገዛ ነበር።
18
እርሱና አባቱ የቀደሱትን ብሩን፣ ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገባ።
19
እስከ ሠላሳ አምስተኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ምንም ዐይነት ጦርነት አልነበረም።
← Chapter 14
Chapter 16 →