bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Chronicles 7
1 Chronicles 7
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ ፉዋ፣ ያሱብ፣ ሺምሮን፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው።
2
የቶላ ወንዶች ልጆች፤ ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበረ።
3
የኦዚ ወንድ ልጅ፤ ይዝረሕያ። የይዝረሕያ ወንዶች ልጆች፤ ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤል፣ ይሺያ፤ አምስቱም አለቆች ነበሩ።
4
ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሯቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ሰዎች ነበሯቸው።
5
ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቍጥር በአጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺሕ ነበሩ።
6
ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል።
7
የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ በአጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺሕ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል።
8
የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።
9
በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺሕ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።
10
የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን። የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳኦር፤
11
እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ ዐሥራ ሰባት ሺሕ ተዋጊዎች ነበሯቸው።
12
ሳፊንና ሑፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ፣ ሑሺም ደግሞ የአሔር ዘር ነው።
13
የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያሕጽሔል፣ ጉኒ፣ ዬጽር፣ ሺሌም፤ እነዚህ የባላ ዘሮች ናቸው።
14
የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው። እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርን የወለደች ናት፤
15
ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር። ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።
16
የሚኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።
17
የኡላም ወንድ ልጅ፤ ባዳን፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው።
18
እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና ማሕላን ወለደች።
19
የሸሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤ አሒያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሒ፣ አኒዓም።
20
የኤፍሬም ዘሮች፤ ሹቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ ልጁ ታሐት፣
21
ልጁ ዛባድ፣ ልጁ ሹቱላ። ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።
22
አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት።
23
ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው።
24
ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት።
25
ልጁ ፋፌ፣ ልጁ ሬሴፍ፣ ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣
26
ልጁ ለአዳን፣ ልጁ ዓሚሁድ፣ ልጁ ኤሊሳማ፣
27
ልጁ ነዌ፣ ልጁ ኢያሱ።
28
ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተ ምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም ዐልፎ ዓያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር።
29
በምናሴም ወሰን ላይ ቤትሳን፣ ታዕናክ፣ መጊዶና ዶር ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር።
30
የአሴር ወንዶች ልጆች፤ ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊ፣ በሪዓ፤ እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።
31
የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ ሐቤርና የቢርዛዊት አባት መልኪኤል።
32
ሔቤርም ያፍሌጥን፣ ሳሜርን፣ ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ።
33
የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ ፋሴክ፣ ቢምሃል፣ ዓሲት፤ የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ።
34
የሳሜር ወንዶች ልጆች፤ አኪ፣ ሮኦጋ፣ ይሑባ፣ አራም።
35
የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ ጾፋ፣ ይምና፣ ሰሌስ፣ ዓማል።
36
የጻፋ ወንዶች ልጆች፤ ሱዋ፣ ሐርኔፍር፣ ሦጋል፣ ቤሪ፣ ይምራ፣
37
ቤጴር፣ ሆድ፣ ሳማ፣ ሰሊሳ፣ ይትራን፣ ብኤራ።
38
የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ ዮሮኒ፣ ፊስጳ፣ አራ።
39
የዑላ ወንዶች ልጆች፤ ኤራ፣ ሐኒኤል፣ ሪጽያ።
40
እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ ምርጥ ሰዎች፣ ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ። በትውልድ መዝገባቸው እንደ ተጻፈው ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቍጥር ሃያ ስድስት ሺሕ ነበር።
← Chapter 6
Chapter 8 →