bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Chronicles 25
1 Chronicles 25
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋር ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገናና በጸናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶታም ቤተ ሰብ መካከል መርጦ መደበ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፤
2
ከአሳፍ ወንዶች ልጆች፤ ዘኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። የአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሡ አመራር ሥር ነበረ።
3
ከኤዶታም ወንዶች ልጆች፤ ጎዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።
4
ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መታንያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ሐናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።
5
እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለ ራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ሰጡት ። እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።
6
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጸናጽል፣ በመሰንቆና በበገና ድምፅ ለሚቀርበው የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሡ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ።
7
እነዚህም ከቤተ ዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑና የተካኑ ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
8
የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።
9
የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ለዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ፤ ቍጥራቸውም 12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቍጥራቸውም 12
10
ሦስተኛው ለዛኩር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
11
አራተኛው ለይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
12
አምስተኛው ለነታንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
13
ስድስተኛው ለቡቅያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
14
ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
15
ስምንተኛው ለየሻያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
16
ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
17
ዐሥረኛው ለሰሜኢ ወጣ፤ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
18
ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
19
ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
20
ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
21
ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
22
ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
23
ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
24
ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
25
ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
26
ዐሥራ ዘጠነኛው ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
27
ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
28
ሃያ አንደኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
29
ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
30
ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12
31
ሃያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12።
← Chapter 24
Chapter 26 →