bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Chronicles 20
1 Chronicles 20
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
ነገሥታት ለጦርነት በሚሄዱበት በጸደይ ወራት፣ ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ ወደ ራባትም ሄዶ ከበባት፤ ዳዊት ግን ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር። ኢዮአብም ራባትን ወግቶ አፈራረሳት።
2
ዳዊት የንጉሣቸውን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ነበረ፤ ይህንም በዳዊት ራስ ላይ ጫኑለት፤ እንዲሁም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።
3
በዚያ የነበረውንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው። ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረገ። ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
4
ከዚያም በኋላ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በጌዝር ጦርነት ተደረገ፤ በዚያ ጊዜ ኩሳታዊው ሴቦካይ የራፋይም ዘር የሆነውን ሲፋይን ገደለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ድል ተመቱ።
5
ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ፤ የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጌት ተወላጅ የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።
6
ደግሞም ጌት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ ይህም እንደዚሁ ከራፋይም ዘር ነበረ።
7
እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
8
በጌት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም በዳዊትና በሰዎቹ እጅ ወደቁ።
← Chapter 19
Chapter 21 →