bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
/
1 Chronicles 14
1 Chronicles 14
Amharic NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
1
በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና ዐናጢዎችን ከዝግባ ዕንጨት ጋር ላከ።
2
ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ አንግሦ እንዳጸናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት አስተዋለ።
3
ዳዊትም በኢየሩሳሌም ብዙ ሚስቶች አገባ፤ ከእነርሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
4
በዚያ ሳለ የወለዳቸው የልጆቹ ስም ይህ ነው፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፣
5
ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
6
ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣
7
ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት።
8
ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ተቀብቶ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ይህን ሰምቶ ስለ ነበር ሊገጥማቸው ወጣ።
9
በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን መጥተው የራፋይምን ሸለቆ ወረሩ።
10
ስለዚህ ዳዊት፣ “ወጥቼ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልን? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ፣ “አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” ብሎ መለሰለት።
11
ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤ በዚያም ድል አደረጋቸው። ዳዊትም፣ “ውሃ ነድሎ እንደሚወጣ ሁሉ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው” አለ፤ ከዚህም የተነሣ ያን ቦታ “በኣልፐራሲም” ብለው ሰየሙት።
12
ፍልስጥኤማውያን አማልክታቸውን በዚያው ጥለዋቸው ስለ ነበር፣ ዳዊት በእሳት እንዲያቃጥሏቸው አዘዘ።
13
ፍልስጥኤማውያን ሸለቆውን እንደ ገና ወረሩ፤
14
ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት “ዙሪያውን ከብበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤
15
በሾላው ዐናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ወዲያውኑ ለጦርነት ውጣ፤ ይህም የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ለመምታት እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቷል ማለት ነውና።”
16
ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ ከገባዖን ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መቷቸው።
17
ከዚህም የተነሣ የዳዊት ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤ እግዚአብሔርም መንግሥታት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።
← Chapter 13
Chapter 15 →