bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Song of Solomon 6
Song of Solomon 6
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ውድሽ ወዴት ሄደ? አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ውድሽ ወዴት ፈቀቅ አለ?
2
ውዴ በገነቱ መንጋውን ያሰማራ ዘንድ አበባውንም ይሰበስብ ዘንድ ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ።
3
እኔ የውዴ ውዴም የእኔ ነው፥ በሱፉ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።
4
ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥ እንደ ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት ታስፈሪያለሽ።
5
አውከውኛልና ዐይኖችሽን ከፊቴ መልሺ፥ ጠጉርሽ ከገለዓድ እንደ ወረደ እንደ ፍየል መንጋ ነው።
6
ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ ሁሉ መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።
7
በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭና ጉንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
8
ስልሳ ንግሥቶች ሰማንያም ቁባቶች ቍጥር የሌላቸውም ቈነጃጅት አሉ።
9
ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ አንዲት ናት፥ ለእናትዋ አንዲት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው ብፅዕት አሉአት፥ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኑአት።
10
ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?
11
የወንዙን ዳር ልምላሜ አይ ዘንድ፥ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደሆነ እመለከት ዘንድ ወደ ለውዝ ገነት ወረድሁ።
12
ሳላውቅ ነፍሴ በከበረው ሠረገላ ላይ አስቀመጠችኝ።
13
አንቺ ሱላማጢስ ሆይ። ተመለሽ፥ ተመለሽ፥ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርሷ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።
← Chapter 5
Chapter 7 →