bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Revelation 13
Revelation 13
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ከዚያም አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።
2
ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉን፥ ዙፋኑንና ትልቅ ሥልጣንን ሰጠው።
3
ከራሶቹም አንዱ ለሞት የሚያደርስ ቁስል ነበረው፤ ለሞት የሚያደርሰውም ቁስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ በመገረም አውሬውን ተከተለ፤
4
ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።
5
ታላቅ ነውርንና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።
6
እግዚአብሔርንም ለመሳደብ፥ ስሙንና ማደሪያውን፥ በሰማይ የሚያድሩትን ለመሳደብ አፉን ከፈተ።
7
ቅዱሳንንም የመዋጋት፥ ድልም የማድረግ ፈቃድ ተሰጠው፤ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።
8
ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ የሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ የምድር ነዋሪዎች በሙሉ ይሰግዱለታል።
9
ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።
10
ለመማረክ የተመደበ ወደ ምርኮ ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ መገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው።
11
ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።
12
በመጀመሪያው አውሬ ስም፥ በሙሉ ሥልጣን ይሠራ ነበር። ወደ ሞት የሚያደርሰው ቁስል ለተፈወሰለትም ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።
13
እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር በሰዎች ፊት እስኪያወርድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን ያደርጋል።
14
በአውሬውም ፊት እንዲያደርግ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቁስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲሠሩ በምድር የሚኖሩትን ያዛቸዋል።
15
የአውሬው ምስል እንዲናገርም ሆነ ለአውሬው ምስል የማይሰግዱትን እንዲያስወግዳቸው ለአውሬው ምስል እስትንፋስ እንዲሰጠው ተፈቀደ።
16
ታናናሾችና ታላላቆች፥ ሀብታሞችና ድሆች፥ ጌታዎችና ባርያዎች ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ ያደርጋል፤
17
የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሰው ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችልም ያደርጋል።
18
ጥበብ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ያስላው፤ የሰው ቍጥር ነውና፤ ቁጥሩም ስድስት መቶ ሥልሳ ስድስት ነው።
← Chapter 12
Chapter 14 →