bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 96
Psalms 96
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥ ምድር ሁሉ፥ ለጌታ ዘምሩ።
2
ለጌታ ዘምሩ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ።
3
ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ፥
4
ጌታ ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ ከአማልክትም ሁሉ በላይ የተፈራ ነውና።
5
የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖቶች ናቸውና፥ ጌታ ግን ሰማያትን ሠራ።
6
ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ውበት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።
7
የአሕዛብ ወገኖች፥ ለጌታ አቅርቡ፥ ክብርና ኃይልን ለጌታ አቅርቡ፥
8
ለስሙ የሚገባ ክብርን ለጌታ ስጡ፥ ቁርባን ያዙ፥ ወደ አደባባዮችም ግቡ።
9
በቅድስናው ስፍራ ለጌታ ስገዱ፥ ምድር ሁሉ በፊቱ ትናወጥ።
10
በአሕዛብ መካከል፦ “ጌታ ነገሠ” በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።
11
ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፥ ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ፥
12
መስክና በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ፥ የዱር ዛፎችም ሁሉ በጌታ ፊት ደስ ይበላቸው፥
13
ይመጣልና፥ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፥ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።
← Chapter 95
Chapter 97 →