bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 92
Psalms 92
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።
2
ጌታን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፥
3
በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት
4
ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
5
አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፥ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና።
6
አቤቱ፥ ሥራህ እንዴት ትልቅ ነው! ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!
7
የማያስተውል ሰው አያውቅም። አላዋቂ አይረዳውም።
8
ኃጢአተኞች እንደ ሣር ቢበቅሉ ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ቢለመልሙ፥ ለዘለዓለም ዓለም እንደሚጠፉ ነው።
9
አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፥
10
አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥ ዓመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና።
11
እንደ ጐሽ አጠነከርከኝ ፥ በአዲስ ዘይትም ቀባኸኝ።
12
ዓይኔም ጠላቶቼን ቃኘች፥ ጆሮዬም በእኔ ላይ የተነሡትን ክፉዎች ሰማች።
13
ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።
14
በጌታ ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
15
ያንጊዜ ገና በሽምግልናም ያፈራሉ ገና ወተታማና አርንጓዴ ሆነው ይኖራሉ።
16
ጌታ ትክክለኛ እንደሆነ ይነግራሉ፥ ዓለቴ ነው፤ በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም።
← Chapter 91
Chapter 93 →