bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 90
Psalms 90
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት። አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።
2
ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነህ።
3
ሰውን ወደ አፈር ትመልሳለህ፥ “የሰው ልጆች ሆይ”፥ ተመለሱ ትላለህ፥
4
ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓት ነውና።
5
ታጥለቀልቃቸዋለህ፥ እንደ ሕልም ናቸው፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ሣር።
6
ማልዶ ያብባል፥ በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።
7
እኛ በቁጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና።
8
የተሰወረውን መተላለፋችንን በፊትህ ብርሃን፥ ምሥጢራችንን በፊትህ አስቀመጥህ።
9
ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመዓትህ አልቀናልና፥ ዘመኖቻችንንም እንደ ትንፋሽ ይሆናሉ።
10
የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፥ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፥ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንጠፋለንና።
11
የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?
12
በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኖቻችንን እንዴት እንደምንቆጥር እንዲህ አስታውቀን።
13
አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ለአገልጋዮችህ ራራ።
14
በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን እንጠግባለን፥ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።
15
መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ አሰኘን።
16
ሥራህ ለአገልጋዮችህ ይታይ፥ ግርማህም ለልጆቻቸው ይሁን።
17
የጌታ አምላካችን ቸርነት በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።
← Chapter 89
Chapter 91 →