bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 88
Psalms 88
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር። ለመዘምራን አለቃ በማኸላት ለመዘመር፥ የይዝራኤላዊው የኤማን ትምህርት።
2
አቤቱ፥ የመድኃኒቴ አምላክ፥ በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ፥
3
ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፥
4
ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ቀርባለችና።
5
ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥ ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ።
6
ለዘለዓለም እንደማታስባቸው፥ እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ በሙታን ውስጥ እንዳሉ የተጣልሁ ሆንሁ፥ እነርሱም ከእጅህ ተለዩ።
7
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጉድጓድ አስቀመጥኸኝ።
8
በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።
9
የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፥ በእነርሱ ዘንድ አጸያፊ አደረግኸኝ፥ ተዘግቶብኛል፥ መውጫም የለኝም።
10
ዐይኖቼም በመከራ ፈዘዙ፥ አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።
11
በውኑ ለሙታን ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህን? ጥላዎችስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን?
12
በመቃብርስ ውስጥ ጽኑ ፍቅርህን፥ እውነትህንስ በጥፋት ስፍራ ይነገራሉን?
13
ድንቅ ሥራህ በጨለማ፥ ጽድቅህም በሚረሳበት ምድር ትታወቃለችን?
14
አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፥ በጥዋት ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትደርሳለች።
15
አቤቱ፥ ነፍሴን ለምን ትጥላለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?
16
እኔ ከታናሽነቴ ችግረኛ ለሞትም የቀረብሁ ነኝ፥ በአስደንጋጭ ነገሮችህ ተሰቃየሁ፤ ምንም አቅም የለኝም።
17
ቁጣህ በላዬ አለፈ፥ አስፈሪ ድርጊቶችህ አደቀቁኝ።
18
ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥ በአንድ ላይም አጥለቀለቁኝ።
19
ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጨለማም ዘመዴ ሆነ።
← Chapter 87
Chapter 89 →