bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 86
Psalms 86
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የዳዊት ጸሎት አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ደሃና ችግረኛ ነኝና።
2
ታማኝ ነኝና ነፍሴን ጠብቅ፥ አምላኬ ሆይ፥ በአንተ የታመነውን አገልጋይህን አድነው።
3
አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ማረኝ።
4
የአገልጋይህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።
5
አቤቱ፥ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህና፥ ጽኑ ፍቅርህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።
6
አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ድምፅ ስማ።
7
ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ።
8
አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥ ሥራህንም የሚመስል የለም።
9
ያደረግሃቸው አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፥ አቤቱ፥ በፊትህም ይሰግዳሉ፥ ስምህንም ያከብራሉ፥
10
አቤቱ፥ ድንቅ የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና።
11
አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፥ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል።
12
አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ለዘለዓለምም ስምህን አከብራለሁ፥
13
ጽኑ ፍቅርህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና።
14
አቤቱ፥ ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፥ የክፉዎችም ማኅበር ነፍሴን ፈለጉአት፥ ላንተም ምንም ቦታ የላቸውም።
15
አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥ ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥
16
ወደ እኔ ተመልከት፥ ራራልኝ፥ ኃይልህን ለአገልጋይህ፥ ማዳንህንም ለአግልጋይቱ ልጅ ለእኔ ስጥ።
17
ለመልካም የሚሆን ምልክትን ከእኔ ጋር አድርግ፥ የሚጠሉኝ ይዩ ይፈሩም፥ አቤቱ፥ አንተ ረድተኸኛልና፥ አጽናንተኸኛልምና።
← Chapter 85
Chapter 87 →