bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 8
Psalms 8
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።
2
አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ ምን ያህል ገናና ነው፥ ክብርህን በሰማዮች ላይ የምታኖር።
3
በጠላቶችህ ምክንያት ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።
4
የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችህን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥
5
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?
6
ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፥ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።
7
በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፥ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥
8
በጎችንም ላሞችንም ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥
9
የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሦች፥ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።
10
አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።
← Chapter 7
Chapter 9 →