bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 73
Psalms 73
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው፥ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ።
2
እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ በአረማመዴም ልወድቅ ትንሽ ቀረኝ።
3
የክፉዎችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4
ለሞታቸው ስቃይ የለውምና፥ ሰውነታቸውም ጤናማ ነው።
5
እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም።
6
ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ሐብላቸው፥ ዓመጽ መጐናጸፊያቸው ሆነ።
7
ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፥ ልባቸውም በቅዥት ተሞላ።
8
በሹፈት ክፉ ነገርን ተናገሩ። ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።
9
በሰማይ ላይ በድፍረት ተናገሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።
10
ስለዚህ ሕዝቤም ወደ እነርሱ ይመለሳሉ፥ ከሞላ ውሃቸውም ይጋታሉ ፥
11
እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለን? ይላሉ።
12
እነሆ፥ እነዚህ ክፉዎቸ ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ሀብታቸውን ያበዛሉ።
13
እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።
14
ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።
15
“እንደዚህ እናገራለሁ” ብል ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።
16
አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ።
17
ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ።
18
በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥ ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።
19
እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።
20
ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ መልካቸውን ትንቃለህ።
21
ልቤ ነድዶአልና፥ ኩላሊቴም ቀልጦአልና፥
22
እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
23
እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።
24
በአንተ ምክር መራኸኝ፥ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።
25
በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ? በምድርስ ከአንተ ጋር ሆኜ ሌላ ምን እሻለሁ?
26
ልቤና ሥጋዬ አለቀ፥ እግዚአብሔር ግን ዘለዓለም የልቤ ኃይልና እድል ፈንታዬ ነው።
27
እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፥ በማመንዘር ከአንተ የሚርቁትን ሁሉ አጠፋኻቸው።
28
ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፥ መጠለያዬም ጌታ ነው ሥራህን ሁሉ እናገር ዘንድ።
← Chapter 72
Chapter 74 →