bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 64
Psalms 64
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2
አቤቱ፥ በሮሮዬ ድምፄን ስማ፥ ከጠላትም ፍርሃት ነፍሴን አድን።
3
ከክፉዎች ደባ፥ ከዓመፀኞችም ብዛት ሰውረኝ።
4
እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ፥ እንደ ፍላጻ መራራ ነገርን ለመወርወር፥
5
ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፥ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም።
6
ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፥ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፥ ማንስ ያየናል? ይላሉ።
7
ዓመፃን ፈለጓት፥ ሲፈትኑም አለቁ፥ የሰው የውስጥ አሳቡና ልቡ የጠለቀ ነው፥
8
እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። ድንገተኛ ፍላጻም ያቈስላቸዋል፥
9
አንደበታቸው ያሰናክላቸዋል፥ የሚያዩአቸውም ሁሉ ይደነግጣሉ።
10
ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም አስተዋሉ።
11
ጻድቅ በጌታ ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል፥ ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ እልል ይላሉ።
← Chapter 63
Chapter 65 →