bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 61
Psalms 61
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።
2
አምላክ ሆይ፥ ጩኸቴን ስማ፥ ጸሎቴንም አድምጥ።
3
ልቤ ተስፋ በቈረጠ ጊዜ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ ከፍ ባለ ዓለት ላይ ትመራኛለህ።
4
በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ፥ መጠጊያዬም ሆነኸኛልና።
5
በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፥ በክንፎችህም ጥላ እጋረዳለሁ፥
6
አቤቱ፥ አንተ ስእለቴን ሰምተሃልና፥ ስምህንም ለሚፈሩ ርስትን ሰጠሃቸው።
7
ለንጉሥ ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ፥ ዓመታቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናሉ።
8
በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም ይኖራል፥ ይጠብቁት ዘንድ ቸርነትንና እውነትን አዘጋጅለት።
9
እንዲሁ ለስምህ ለዘለዓለም እዘምራለሁ ስእለቴን ሁልጊዜ እፈጽም ዘንድ።
← Chapter 60
Chapter 62 →