bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 56
Psalms 56
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ ከቅዱሳን ስለ ራቁ ሕዝብ፥ ፍልስጥኤማውያን በጋት በያዙት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
2
አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ማረኝ፥ ሁልጊዜም ተዋጊ አስጨንቆኛል።
3
የሚዋጉኝ በዝተዋልና ቀኑን ሁሉ ጠላቶቼ ረገጡኝ።
4
እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ።
5
በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፥ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሥጋ ምን ያደርገኛል?
6
ሁልጊዜ ቃሎቼን ይጠመዝዙብኛል፥ በእኔ ላይም የሚመክሩት ሁሉ ለክፉ ነው።
7
ይሸምቁብኛል ይሸሸጋሉ፥ ተረከዜን ይከታተላሉ፥ ነፍሴንም ለማጥፋት ይጠብቃሉ።
8
መቼም አታድናቸውም! አቤቱ አሕዛብን በቁጣ ጣላቸው።
9
አምላክ ሆይ፥ መዋተቴን ነገርሁህ፥ እንባዬን በአቁማዳ ውስጥ አኑር።
10
በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፥ አንተ አምላኬ ከእኔ ጋር እንደሆንህ እነሆ፥ አወቅሁ።
11
በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፥ በጌታ ቃሉን እወድሳለሁ።
12
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
13
አቤቱ፥ በአንተ ዘንድ ሰእለት አለብኝ፥ የምስጋና መሥዋዕት አቀርብልሀለሁ፥
14
ነፍሴን ከሞት፥ እግሮቼን ከመውደቅ አድነሃልና፥ በሕያዋን ብርሃን በእግዚአብሔር ዘንድ እመላለስ ዘንድ።
← Chapter 55
Chapter 57 →