bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 36
Psalms 36
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የጌታ ባርያ የዳዊት መዝሙር።
2
ኃጢአተኛ በራሱ የሚያስት ነገርን ይናገራል፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዐይኖቹ ፊት የለም።
3
እራሱን ሸንግሎአልና፥ ኃጢአቱን መቀበልና መጥላት ይሳነዋል።
4
የአፉ ቃል ግፍና ሽንገላ ነው፥ ማስተዋልን በጎ ማድረግንም ተወ።
5
በመኝታው ጠማማነትን አሰበ፥ መልካም ባልሆነች መንገድ ቆሞአል፥ ክፋትን አይቃወማትም።
6
አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ በሰማይ ነው፥ ታማኝነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች።
7
ጽድቅህም እንደ እግዚአብሔር ተራሮች፥ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ናት፥ አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ።
8
አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።
9
ከቤትህ ሙላት ይጠግባሉ፥ ከተድላህም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ።
10
የሕይወት ምንጭ በአንተ ዘንድ ነውና፥ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
11
ጽኑ ፍቅርህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም ልባቸው በቀና ላይ ዘርጋ።
12
የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የዐመጸኞችም እጅ አያስተኝ።
13
ዓመፃን የሚያደርጉ ሁሉ ከዚያ ወደቁ፥ ወድቀዋል፥ መቆምም አይችሉም።
← Chapter 35
Chapter 37 →